Mon – Fri: 8:30 AM – 5:30 PMinfo@ethiopianchamber.com
Latest
አለም አቀፍ የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ እሁድ፣ ህዳር 6 (November 15) በቡና መገኛዋ በጅማ ከተማ በድምቀት ይካሄዳል።የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና የዓለም ባንክ የጋራ ትብብር ለማጠናከር ተወያዩ።የኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት መደበኛ ስብሰባችንን አጠናቀናል።Walgahii idilee Mana Maree Daldalaa fi woldaa sektera Oromiyaa kurmaana jalqabaa bara baajataa 2019, kan har’a ganama magaalaa Adamaatti jalqabne xumurree jirra.በሴቶች አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅርቦት እና የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ሥምምነት ዙሪያ ያተኮረ ወርክሾፕ ተካሄደ።የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ምክር ቤቱ በድሬዳዋ ያደረገውን ቆይታ አስመልክቶ መልዕክት አስተላለፉ።
ECCSA logoECCSAEthiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ምክር ቤቱ በድሬዳዋ ያደረገውን ቆይታ አስመልክቶ መልዕክት አስተላለፉ።

የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ምክር ቤቱ በድሬዳዋ ያደረገውን ቆይታ አስመልክቶ መልዕክት አስተላለፉ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ምክር ቤቱ በድሬዳዋ ያደረገውን ቆይታ አስመልክቶ መልዕክት አስተላለፉ።

ፕሬዚደንቱ በመልዕክታቸው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ ስብሰባችንን እንዲሁም ከድሬዳዋ አስተዳደርና ከድሬዳዋ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አመራሮች ጋር ያደረግነውን ውይይት በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል ብለዋል።

ፕሬዚደንቱ አክለውም በሁለት ቀናት ቆይታችን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን፣ በእቅድ አፈጻጸም ሂደት የተገኙ መልካም ስኬቶችንና የተለዩ የአፈፃፀም ተግዳሮቶችን እንዲሁም በቀጣይ በትኩረት ሊከናወኑ የሚገቡ የቅድሚያ ቅድሚያ ተግባራትን በመለየት በጥልቀት ገምግመናል፤ የተግባራት አፈፃፀም አቅጣጫዎችንም አስቀምጠናል።

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተገኘውን ተሞክሮ ለቀጣይ ስራዎቻችን እንደ ግብዓት በመጠቀም በዚህም የእቅዶቻችንን አፈጻጸም ይበልጥ በማሻሻል እና የስራ ቅድሚያዎችን በግልጽ በመለየትና የሚጠበቀውን ውጤት ተጨባጭ በማድረግ ረገድ ልንሰራ ይገባል።

በተለይም አሁን እያደረግነው ካለነው ጥረት ባሻገር የዴሬክተሮች ቦርዱም ሆነ አመራሩ በጋራ ራዕይ እና በቅንጅት በመስራት ከመደበኛ የስራ አፈጻጸም ባለፈ ተጨባጭ ለውጥና ዘላቂ ተጽዕኖ በሚፈጥሩ ተግባራት ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለብን አረጋግጠናል።

በድሬዳዋ በነበረን ቆይታ ከዚህ በተጨማሪም ፣ ከከተማው አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አብዱላሂ አደም ዩሱፍ እና ከከተማው አመራሮች እንዲሁም ከንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቦርድ አመራሮች ጋር ባደረግነው ውይይት፣ የምክር ቤቱን ተቋማዊ አቅም ለማጠናከር፣ የአባላትን ተሳትፎ ለማሳደግና የግሉ ዘርፍን ጥቅም በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ በሚያስችሉ የትብብር ተግባራት ላይ ሀሳብ ተለዋውጠናል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከድሬዳዋ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ፍላጎት በመግለጽ፣ አቅሙ በፈቀደው መጠን ምክር ቤቱን ለመደገፍና የሚኖረውን የጋራና የትብብር ስራዎች ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጦልናል። የከተማው አስተዳደር ላሳየው ለዚህ አብሮ የመስራት ቁርጠኛነትና ፍላጎት ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በኩልም የድሬዳዋ ንግድ ምክር ቤት ተቋማዊ አቅሙን እንዲያጠናክር፣ የአባላትን ፍላጎት እንዲያሟላ ፣ከሚጠበቅበት ሚና ጋር የሚጣጣም ውጤታማ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ የሚያስችሉ የድጋፍና የትብብር ስራዎችን እጠናክረን የምንቀጥልበት ቁልፍ ስራችን ይሆናል።

በመጨረሻም፣ በከፍተኛ መስተንግዶ የታጀበ የስራ ቆይታችንን ውጤታማና የተሳካ ላደረጉልን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አብዱላሂ አደም ዩሱፍ እና የከተማውን አመራሮች እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቦርድ አመራሮችና ሌሎች ሰራተኞችን በራሴ እና በምክር ቤታችን የዴሬክተሮች ቦርድ ስም አመሰግናለሁ ሲሉ አጠቃለዋል።