Mon – Fri: 8:30 AM – 5:30 PMinfo@ethiopianchamber.com
ECCSA logoECCSAEthiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ ስብሰባችን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ ስብሰባችን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ ስብሰባችንን እንዲሁም ከድሬዳዋ አስተዳደርና ከድሬዳዋ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አመራሮች ጋር ያደረግነውን ውይይት በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል።

በሁለት ቀናት ቆይታችን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን፣ በእቅድ አፈጻጸም ሂደት የተገኙ መልካም ስኬቶችንና የተለዩ የአፈፃፀም ተግዳሮቶችን እንዲሁም በቀጣይ በትኩረት ሊከናወኑ የሚገቡ የቅድሚያ ቅድሚያ ተግባራትን በመለየት በጥልቀት ገምግመናል፤ የተግባራት አፈፃፀም አቅጣጫዎችንም አስቀምጠናል።

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተገኘውን ተሞክሮ ለቀጣይ ስራዎቻችን እንደ ግብዓት በመጠቀም በዚህም የእቅዶቻችንን አፈጻጸም ይበልጥ በማሻሻል እና የስራ ቅድሚያዎችን በግልጽ በመለየትና የሚጠበቀውን ውጤት ተጨባጭ በማድረግ ረገድ ልንሰራ ይገባል።

በተለይም አሁን እያደረግነው ካለነው ጥረት ባሻገር የዴሬክተሮች ቦርዱም ሆነ አመራሩ በጋራ ራዕይ እና በቅንጅት በመስራት ከመደበኛ የስራ አፈጻጸም ባለፈ ተጨባጭ ለውጥና ዘላቂ ተጽዕኖ በሚፈጥሩ ተግባራት ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለብን አረጋግጠናል።

በድሬዳዋ በነበረን ቆይታ ከዚህ በተጨማሪም ፣ ከከተማው አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አብዱላሂ አደም ዩሱፍ እና ከከተማው አመራሮች እንዲሁም ከንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቦርድ አመራሮች ጋር ባደረግነው ውይይት፣ የምክር ቤቱን ተቋማዊ አቅም ለማጠናከር፣ የአባላትን ተሳትፎ ለማሳደግና የግሉ ዘርፍን ጥቅም በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ በሚያስችሉ የትብብር ተግባራት ላይ ሀሳብ ተለዋውጠናል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከድሬዳዋ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ፍላጎት በመግለጽ፣ አቅሙ በፈቀደው መጠን ምክር ቤቱን ለመደገፍና የሚኖረውን የጋራና የትብብር ስራዎች ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጦልናል። የከተማው አስተዳደር ላሳየው ለዚህ አብሮ የመስራት ቁርጠኛነትና ፍላጎት ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በኩልም የድሬዳዋ ንግድ ምክር ቤት ተቋማዊ አቅሙን እንዲያጠናክር፣ የአባላትን ፍላጎት እንዲያሟላ ፣ከሚጠበቅበት ሚና ጋር የሚጣጣም ውጤታማ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ የሚያስችሉ የድጋፍና የትብብር ስራዎችን እጠናክረን የምንቀጥልበት ቁልፍ ስራችን ይሆናል።

በመጨረሻም፣ በከፍተኛ መስተንግዶ የታጀበ የስራ ቆይታችንን ውጤታማና የተሳካ ላደረጉልን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አብዱላሂ አደም ዩሱፍ እና የከተማውን አመራሮች እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቦርድ አመራሮችና ሌሎች ሰራተኞችን በራሴ እና በምክር ቤታችን የዴሬክተሮች ቦርድ ስም አመሰግናለሁ።

የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት