የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ የምክር ቤቱን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያዉን ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ገምግሞ የቀጣዩን ሩብ ዓመት የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል።
የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት የተከበሩ አቶ ሰብስብ አባፊራ የምክር ቤቱ የመጀመሪያዉ ሩብ ዓመት አፈፃፀም አበረታች መሆኑን ገልፀዉ በተለይም የዳይሬክተሮች ቦርድ ካስቀመጣቸዉ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ግቦች አንፃር ሲታይ የታቀዱ ተግባሮችና ክንዉናቸዉ ሪፎርሙን በታቀደለት ጊዜና መሠረት ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚቻል አመላካች ናቸዉ ብለዋል።
ይህ አበረታች ዉጤት ሊመዘገብ የቻለዉ ምክር ቤቱ ተግባራዊ ባደረገዉ ሪፎርም መሠረት ስራና ሠራተኛን ማገናኘት በመቻሉ ነዉ ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
የምክር ቤቱ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በሰጡት አስተያየት በቀሪዉ የበጀት ዓመቱ ጊዜም የታቀዱ ተግባራት በታቀዱት መሠረት እንዲከናወኑ አስፈላጊዉን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ አፅንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል።

