የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና የዓለም ባንክ በቢዝነስ ለሰላም እና በዘላቂ የልማት ሥራዎች ዙሪያ የጋራ ትብብር ለማጠናከር ተወያዩ።
ምክር ቤቱ ምቹና ለንግድ ሥራ ተስማሚ የሆነ የንግድና ኢንቨስትመንት አካባቢ ለመፍጠር ከዓለም ባንክ ጋር ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ያለውን ፍላጎትም የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ሔለን ረታ ገልፀዋል።
በዓለም ባንክ የግሉ ዘርፍ ባለሙያ ወ/ሮ ማርያማዊት እንግዳወርቅ በበኩላቸው ባንኩ ከምክር ቤቱ ጋር በመተባበር የግሉን ዘርፍ ለመደገፍ ሊሠራባቸው ስለሚችሉ የትብብር መስኮች አብራርተዋል።

